KG

Cruise School has four kindergartens in Nifas Silk Lafto & Kolfe Keranio Subcity. The first kg was established in 1987 E.C. & is situated in Kolfe keranio Subcity, woreda 09. All kg campuses has spacious and conveniently located to accommodate the learning teaching process and serves as a playground for the kids. The campuses have class rooms, offices, napping rooms for the kids, pedagogical, first aid, staff, dinning, cafeteria & rest rooms.

All the kgs are equipped with teachers & assistant teachers who have long experience & love working with kids. The kids based on their age group are offered a curriculum which allows them to observe & understand their environment, and develop different skills. In addition, they take part in different clubs to develop their perception & learn through doing. We have Play, entertainment, environmental science, language, mini media, question & answer & compound beautification clubs for the children & their teachers to participate.

ክሩዝ ትምህርት ቤት አራት የአፀደ ሕፃናት ትምህርት ቤቶች ያሉት ሲሆን በኮልፌ ቀራንዮ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው ትምህርት ቤት በ1987 ዓ.ም. የተመሰረተ ሲሆን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የሚገኝ ነው፡፡ ሁሉም ት/ቤቶች ሰፋፊ ምድረ ግቢ ያላቸውና ለሕፃናቱ ለመማሪያም ሆነ ለመጫወቻ በቂና የተመቹ ናቸው፡፡ በውስጣቸውም የመማሪያ ክፍሎችን፣ የር/መምህር ቢሮዎችን፣ የሕፃናቱ የማሸለቢያ፣ የማበልጊያ፣ የመጀመሪያ ሕክምና መስጫ፣ የመምህራን ማረፊያ፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የካፍቴሪያና የመፃዳጂያ ክፍሎችን የያዙ ናቸው፡፡

የአፀደ ሕፃናት ት/ቤቶቻችን በበርካታ ሕፃናትን ከልባቸው በሚወዱና የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው መምህራንና ረዳት መምህራን የተሞላ ነው፡፡ ሕፃናቱም እድሜያቸውን ያገናዘበና አካባቢያቸውን ለመረደትና ለመገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ችሎታዎችን ለመቅሰም የሚያስችላቸውን ትምህርት ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የበለጠ ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ ሲባል በተለያዩ ክበቦች አማካኝነት የተለያዩ ነገሮችን ማድረግን ከመምህራኖቻቸው ጋር በተሳትፎ ይማራሉ፡፡ ክበቦቻችንም የጨዋታ፣ የመዝናኛ፣ የአካባቢ ሳይንስ፣ የቋንቋ፣ የሚኒ ሚዲያ፣የጥያቄና መልስ እና የግቢ ውበት ክበቦች ናቸው፡፡