Secondary & Preparatory

Cruise school Gabriel campus is the secondary high school campus established in 2001 E.C. is located in N/S/ Lafto Sub city woreda 03, opposite Dil Gebeya, next to Save the Children. The campus mainly has a three floor building which accommodates administrative offices, class rooms, Science &IT labs, and library. Additional buildings are suited which provide services like, record office, store, first aid room, pedagogical center, staff room & staff & student cafeteria.

The library selves hundreds of books & thousands of e-books almost all required reference books both for students & teachers. The Biology, Chemistry & Physics laboratories are fully equipped with the required laboratory specimens, chemicals, regents, and apparatus to allow our students see, observe, discover or relate practically what they have learnt theoretically in class rooms. Especially our Physics lab is equipped with the latest state of the art imported from abroad through the fund secured from the USA Embassy in Ethiopia. The grant also offered our physics teachers training on the manipulation of the instruments acquired.

We have an IT lab which allows our students to develop their knowledge & skills in Computer Science. Last but not least, the pedagogical center is where our students & teachers develop teaching aids & materials like diagrams, tables, charts, maps, and 3D models which assist our teachers to conduct the teaching learning process. It also lays the means for students to be innovative & come up with creative works & supports them to participate in regional Science fair competitions.

የክሩዝ ትምህርት ቤት የገብርኤል ግቢ የሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርትን የሚሠጥ ግቢ ሲሆን በ2001 ዓ.ም. የተመሰረተ ሲሆን፤ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ከድል ገበያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ ከሴቭ ዘችልድረን ዋና መ/ቤት አጠገብ ይገኛል፡፡ ይህ ግቢ በዋናነት ባለ 3 ፎቅ ሕንፃ ያለው ሲሆን ይህም የአስተዳደር ቢሮዎችን፣ የመማሪያ ክፍሎችን፣ የሳይንስና የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራዎችንና ቤተ-መፃህፍትና ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም የመዝገብ ቤት፣ የድንገተኛ ህክምና ክፍል፣ የመምህራንና የተማሪዎች ካፍቴሪያ እንዲሁም የትምህርት ማዕከል በመሆን የሚያገለግሉ ተጨማሪ  ሕንፃዎች አሉት፡፡

ቤተ-መፃሕፍታችን በበርካታ መቶዎች በሚቆጠሩ የትምህርት መፃሕፍትና በሺዎች የሚቆጠሩ  e-books ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን አቅርቧል፡፡ የባዮሎጂ፣ የኬሚስትሪና የፊዚክስ ቤተ-ሙከራዎቻችን በከፍተኛ ሁኔታ የተደራጁና በተገቢዎቹ ንጥረ ነገሮች፣ ኬሚካሎችና መሳሪያዎች የተሟላ ሲሆን ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ  የተማሩትን ወደ ተግባር በመለወጥ በተግባር የሚሞክሩበትና የሚመራመሩበት ነው፡፡ በተለይም በፊዚክስ ቤተ-ሙከራችን ከአሜሪካን ኤንባሲ ባገኘነው እርዳታ አለም የደረሰበትን የመጨረሻውን የመጨረሻውን ቴኬኖሎጂ መጠቀም አስችሎናል፡፡ እርዳታው የፊዚክስ መምህራኖቻችንንም የመሳሪያውን አጠቃቀምና አተገባበር ስልጠናንም ያካተተ ነበር፡፡

የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራችን ተማሪዎቻችን የኮምፒውተር ሳይንስ እውቀትና ችሎታቸውን ያዳብሩ ዘንድ አስችሎዋቸዋል፡፡ እንዲሁም የትምህርት ማዕከላችን ተማሪዎችና መምህራን የመማር ማስተማሩን ሂደት አጋዥ መሳሪያዎችን ለማምረት የሚያስችላቸው ሲሆን፤ በዚሁ ክፍል ውስጥ የተለያዩ ትምህርታዊ ስዕሎችን፣ የመረጃ ሳጥኖች፣ ካርታዎች እንዲሁም 3D  ሞዴሎች ያመርቱበታል፡፡ ይህ ማዕከል ተማሪዎች የፈጠራ ችሎታቸውን የሚያዳብሩባቸውና በተለያዩ ሳይንሳዊ ውድድሮች ሲሳተፉ የፈጠራ ስራዎችን ለማምረት ያግዛቸዋል፡፡