Middle(1-4)






Cruise school has 2 middle school Campuses (grades1-4) located in N/S/Lafto subcity, woreda 03.The campuses are filled with highly experienced teachers & administrative staff. The campuses learning from its experience, provides continuous trainings for directors & deputy directors of all the other campuses of the school.
The campuses evaluate their reference books annually & publish improvised books based on the needs & the potential of their students. Hence, we have succeeded in increasing the interest of students to learn & in creating a healthy environment of competition among students. Besides, we have implemented a regular program to assist students with lower grades through various award systems.
The campuses ensure the participation of students in various clubs & color houses, so as to help them develop all rounded personality. Students are enrolled in one or two of our clubs which include, gender, health, environmental care & prevention, sports, art, language, science & technology, ethics & moral, social affairs, social science, student organization, & tomorrow’s person. Besides, they took part in one of the four color houses (green, white, yellow & blue), are enabled to nurture their natural skills & talents.
The passion of our teachers & assistant teachers, the family like relationship they have with their students & parents, the convenient learning teaching process & the attractive working environment make our campuses unique. The campuses dispense their social & national responsibility through participation in green & clean environment initiatives, traffic safety, development of pedestrian walk ins, road sides & street dividers, fund raising for disadvantaged citizens & local NGOs who work to this end.



ክሩዝ ት/ቤት የአንደኛ ደረጃ ቁጥር 2 ግቢ 15 የመማሪያና 8 የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች የያዘ፣ እድሜያቸው ከ7-10 ዓመት የሆኑና ከ1ኛ እስከ 4ኛ የክፍል ደረጃ ላይ የሚገኙ ወንድ 244 ሴት 218 በድምሩ 462 ተማሪዎች አሉት፡፡ በምድረ ግቢው ሶስት ብሎኮች ያሉት እና በ#ሀ; ፊደል ቅርፅ ዙሪያውን ጥግ ይዞ የሚገኝና መሃሉ ለተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች የሚደረግበት ሜዳ ያለው ነው፡፡ ት/ቤቱ ከፍተኛ የት/ት ደረጃ እና ልምድ ባላቸው የት/ቤቱ አስተዳደር መምህራን፣ የጠቅላላ አገልግሎት ሰራተኞች የተዋቀረ ሲሆን ፣ ከግዜ ወደ ጊዜ ባሳየው ለውጥ ከኬጂ 2 ጀምሮ ያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች እስከ 4ኛ ክፍል እና ከዚያም በላይ በማድረስ አሁን ያለበት ደረጃ ሊደርስ ችሏል፡፡
ት/ቤቱ ከራሱ ግቢ ልምድና ተሞክሮ በመነሳት ለሁሉም ግቢ ረ/መምህራንና ለመምህራን ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት ለመማር ማስተማር ሂደቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል፡፡ ት/ቤቱ ከዚህም በተጨማሪ በየዓመቱ የመማሪያ መፅሃፍትን በመገምገምና በማሻሻል የተማሪዎቹን የመማር አቅምና ፍላጎትን ያገናዘቡ መፅሃፍችን ማሳተም ችሏል፡፡ ት/ቤቱ የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት ለማሳደግ እና በተማሪዎች ዘንድ ጤናማ የውድድር መንፈስ መፍጠር ችሏል፡፡ የተለያዩ የሽልማት ስርዓቶችን ዘርግቶ በውጤታቸው ዝቅ ያሉ ተማሪዎችን የማብቃት ስራዎችን በመደበኛት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ት/ቤቱ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የተማሪዎችን ሁለንተናዊ እድገት በማረጋገጥ በተለያዩ ክበባት እና ሃውሶች ውስጥ እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡ ተማሪዎቹም ካሉት ክበባት ማለትም የስርዓተ-ፆታ ክበብ፣ የጤና ክበብ፣ የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ክበብ ፣ የሰውነት ማጎልመሻ ክበብ፣ የኪነ-ጥበብ ክበብ፣ የቋንቋ ክበብ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ፣ የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ክበብ፣ የማህበራዊ አገልግሎት ክበብ፣ የህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ፣ የተማሪ አደረጃጀት ክበብ፣ የነገው ሰው ክበብ ውስጥ በአንድ ወይም በሁለት ክበባት እንዲሁም ካሉት አራት የቀለማት ቤቶች ማለትም አረንጓዴ የቀለም ቤት፣ ነጭ የቀለም ቤት፣ ቢጫ የቀለም ቤት፣ ሰማያዊ የቀለም ቤት በአንዱ አባል በመሆን ያላቸውን ተሰጥኦ እንዲያዳብሩ ይደረጋል፡፡
የረ/መምህራንና የመምህራን ቁርጠኝነት ተነሳሽነት ከተማሪና ከወላጆች ጋር ባለው ቤተሰባዊ ግንኙነት መልካም የመማር ማስተማር ሂደት እና ጥሩ የስራ አካባቢ መፍጠር መቻሉ ት/ቤቱን ልዩ ያደርገዋል፡፡ ት/ቤቱ በአካባቢ ንፅህና ልማት፣አረንጓዴ ልማት፣በትራፊክ ደህንነት፣አደባባዮችንና መንገድ አካፋዮችን በማልማት ፣ለተቸገሩ ወገኖች በአይነትና በገንዘብ እንዲሁም በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ለተሰማሩ ተቋማት እና ለተለያዩ ድርጅቶች የእርዳታ መዋጮ/ድጎማ በማከናወን ሃገራዊና ማህበራዊ ሃላፊነቶቹን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡


